Sunday, March 18, 2012

የዋልድባ ገዳም አበምኔት ቤት በፌዴራል ፖሊስ ፍተሻ ተካሄደበት

· አበምኔቱ መምህር ገብረ ጊዮርጊስ ገብረ አረጋዊ ያሉበት አልታወቀም።
· የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ልኡካን ጠንካራ ተቃውሞ እየገጠማቸው ነው።
 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 8/2004 .ም፤ ማርች 17/2012) በዋልድባ ገዳማት ህልውና እና ክብር ላይ ከተፈጠረው ችግር ጋራ በተያያዘ ወደ ስፍራው ያመሩት ሁለት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎች በዓዲ አርቃይ ስብሰባ ማድረጋቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ እና የሕዝብ ግንኙነት መመሪያ ሓላፊው አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ በዓዲ አርቃይ ከገዳሙ ማኅበር ተወካዮች ጋራ ያደረጉት ውይይት የገዳሙን ተወካዮች በጫና ውስጥ በሚያስገባ አኳኋን በመንግሥት የተወጠነውን ዕቅድ አሳምኖልማቱን በማስቀጠልላይ ብቻ ያተኰረ እንደ ነበር ተጠቁሟል፡፡



ይኹንና በውይይቱየታሰበው ሳይሳካ ቀርቷልያሉት ምንጮቹ ከስብሰባው በኋላ በውይይቱ ላይ ያልነበሩት የገዳሙ አበምኔት ቤት በፌዴራል ፖሊስ እና ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቀዳሚ ውይይት ከተካሄደበት ማይ ፀብሪ በመጡ ባለሥልጣናት ፍተሻ እንደተካሄደበት ተዘግቧል፡፡ የመረጃው ምንጮች አበምኔቱ መምህር ገብረ ጊዮርጊስ ገብረ አረጋዊ ያሉበት ትክክለኛ ቦታ ለጊዜ እንደማይታወቅ ለደጀ ሰላም ገልጸዋል፡፡

ዋልድባ እንዲህ ባለ ችግር ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት ቅዱስ ሲኖዶስ እና ፓትርያርኩ ምን እያደረጉ ነው የሚለው ጥያቄ ከፍ ብሎ መሰማት ጀምሯል። አንዳንዶችምአባ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያኒቱን እያጠፏት ነውየሚለውን ወደማመኑ እየደረሱ ነው። 16 ዓመት በፊት የዋልድባ አብረንታንት ገዳምን የጎበኙት አቡነ ጳውሎስሴቶችና ወንዶች በአንድነት የሚቆርቡበት ቤተ ክርስቲያን ይሠራበሚል የሰጡት መመሪያ ከፍተኛ ተቃውሞ ቀስቅሶ ነበር፡፡ መመሪያው በገዳማውያኑ ጸሎት እና ለፓትርያሪኩ በቀጥታ በተጻፈላቸው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተፈጻሚነት አለማግኘቱ ቢገለጽም አሁን የሚታየው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዳተኝነት የዚህ ክትያ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ 

በወቅቱ (1989 .) አበምኔቱ በገዳሙ ክልል ውስጥ በሚካሄደው የከብት ስምሪት እና በየዓመቱ በሚያጋጥመው ሰደድ እሳት ሳቢያ ቅዱሳኑ እየተረበሹ፣ የዱር እንስሳቱም እየተሰደዱ የመሆኑን ችግር ለፓትርያርኩ አመልክተው ነበር፡፡ 

1989 . በከፍተኛ የጥበቃ አጀብ በገዳሙ ተገኝተው የነበሩት አቡነ ጳውሎስ እንደ አንድ ድርጎኛ ተቆንነዋል፤ በአብያተ ምርፋቁ ቋርፍ ተመግበዋል፣ ጭልቃ ጠጥተዋል፤ ሕጽበተ እግር ተደርጎላቸው ማየ ዮርዳኖስን ቀምሰዋል፤ ከገዳሙ ሥምረት ገብተው መቁጠሪያተቀብለዋል፡፡ ለመናንያኑና አገልጋይ መነኰሳቱ የረዱት 50,000 ብር ግንኀምሳ ሺሕ ጣጣ ያመጣብናልበሚልይቅርብንአሰኝቶ ነበር፡፡ 

ስለ ዋልድባ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን እንደ ደረሰን እናቀርባለን፡፡









ቸር ወሬ ያሰማን



አሜን፡፡

6 comments:

  1. Please also update us about the fire @ ዝቋላ

    ReplyDelete
  2. ቸር ወሬ ያሰማን

    ReplyDelete
  3. አምላክ ሆይ ስማን!

    ReplyDelete
  4. Egziabher hoy atetewen sewu seten!

    ReplyDelete
  5. አሁንስ በዛ መንግስት እራሱ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ለማጥፋት ከፍተኛ የሆነ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ስለዚህ እባካቸሁ ህዝበ ክርስቲያኑ መሮታል የሚቻላችሁን ሁሉ አድረጉ፡፡ለምን ሰልፍ አንወጣም; እኛ ዝም ስላልን እኮ ነው ይሄ ሁሉ ስራ የሚሰራብን፡፡ አንዲ ነገር ልንገራችሁ አቡነ ፓውሎስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን አይጠቅማትም፡ እሳቸው የፖለቲካ ስው ናቸው፡፡የኢህአደግን አላማ እንጂ፡ የቅድስት ቤተክርስቲያንን አላማ አያራምዱም፡፡ብቻ……………………………………………….እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

    ReplyDelete