Friday, March 16, 2012

‹‹ራሳችንን ለሰይፍ አዘጋጅተን የተቀመጥን ሰዎች ነን›› የዋልድባ መነኮሳት

  • እኛ በዚህ ያለነው ማህበረ መነኮሳት አቅም የለንም ማድረግ የምንችለው ለሰይፍ ተዘጋጅተን መቀመጥ ብቻ ነው እኛን ገድላችሁ ፋብሪካውን መስራት  ችላላችሁ
  • እናንተ የፈለጋችሁትን ማድረግ ትችላላችሁ ፤ እኛ ይግባኝ ለክርስቶስ ሰጥተናል››   
(አንድ አድርገን መጋቢት 7 ፤ 2004ዓ.ም)፡- ከቀናት በፊት በመንግስትና በዋልድባ ገዳም መካከል ስላለው ውዝግብ መረጃ  አቅርበን ነበር ፤ አሁን እንደሰማነው ቅዳሜ 01/07/2004ዓ.ም እና ማክሰኞ 04/07/2004ዐ.ም በሽሬ ከመንግስት የተወጣጡ ከፍተኛ ባለስልጣናት የገዳሙን አባቶች ለማነጋገር ፕሮግራም ይዘው ነበር ፤ ነገር ግን ከአባቶች በኩል በእዚያ ያሉ ሰዎች ለእኛ ጥሩ አመለካከት የላቸውም ስለዚህ በአማካይ ቦታ በአድርቃይ ስብሰባውን እናድርግ ያሉ ሲሆን በዚህ ተስማምተው ስብሰባውን አድርቃይ አድርገዋል፡፡
·        ከቤተክህነት የተወከሉት አባት እንዴት ይህን ጉዳይ እኛ ሳናቀው የግል መገናኛ ብዙሀን ጋር ይዛችሁ ትሄዳላችሁ ይህ አግባብ ነው ወይ ? የሚል ጥያቄ የተጠየቁ ሲሆን የዋድባው አንድ አባት ‹‹መንግስት ለመገናኛ ብዙሀን የመፃፍም ሆነ የመናገር መብት እስከሰጣቸው ድረስ እኛ ጉዳዩን የፈለግነው ጋር ይዘን እንሄዳለን ፤ መብታችን ነው›› የሚል መልስ ሰጥተዋል ፤ መገናኛ ብዙሀን የህዝብን ድምጽ ተቀብሎ ለህዝብ እንዲያደርስ ፍቃድ ተሰጠው ህጋዊ ተቋም ነው ፤ እኛ ምንም ያጠፋነው ነገር የለም ፤ ቤታችን ሲፈርስ መሬታችን ሲታረስ እያየን ቤተክርነቱን መጠበቅ አይጠበቅብንም ተብለዋል ፤ ‹‹ነጻ ሚዲያ እስካለ ድረስ ጉዳዩን ነጻ ሚዲያ ላይ ማውጣት ህገ መንግስታዊ መብታችን  ነው›› ብለዋል፡
  • በተጨማሪ ከቤተክህነት የተወከሉ ሰው የዋልድባው አባት በሰጡት ሀሳብ ላይ ይህ የቤተክርስትያ አስተምህሮ አይደለም  ፤ ጉዳዩን አንድ ላይ ሆነን ነበር መንግስት ዘንድ ማቅረብ የነበረብን ሲሉ ፤ ‹‹ እናንተማ ቤተክርስትያኗን ለመንግስት አሳልፋችሁ ለመስጠት ፤ ከመንግስት ጎን ተሰልፋችሁ መጣችሁ ይህን ጉዳይ ከናንተ ጋር ሆነን መንግስት ዘንድ ይዘን መቅረብ አንችልም ፤ እናንተ ሲጀምር ለቤተክርስትያን ህልውና የቆማችሁ አይደላችሁም›› ተብለዋል፤  ከተሰብሳቢ አባቶች በኩል ተገቢ አፍ የሚያስይዝ መልስ ተሰቷቸዋል ፤

አይ ቤተክህነት ከአባቶች ጎን ቆሞ መንግስት ጋር ተገቢውን ጥያቄ ይዞ በመቅረብ ለዚህ የጭንቅ ጊዜ አጋር እደመሆን የራሷን አቋም ይዛ ከአባቶች ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ መግባት ምን ይሉታል?  ገዳም ያሉ አባቶች ለነፍሳቸው ያደሩ መሆናቸው ዘነጋችኋቸው እንበል?  ቤተክህነት የራሱን ውሳጣዊ ችግር ሳይፈታ ይህን የሚያህል ቤተክርስትያን ላይ ያጋረጠን ክፉ ጊዜ ማለፊያ መንገድ ይጠቁማል  ማለት ዘበት ነው ፤ ለነፍሳቸው ያደሩ አባቶች ከአምላካቸው ጋር ይፈቱታል ለእናንተ ለስጋውያን ግን ትንሽ ከበድ ይላል፡፡ 
 ይህ ጉዳይ ለቢዮንሴ ወረብ ማስወረብን ያህል የቀለለ አይደለም ፤ ቆም ብላችሁ ተመልከቱ ፤ ነገንም አስተውሉ ፤ ከቤተክርስትያን ዘንድ ብቻም ወግኑ ፤ እናንተ ሀላፊነታችሁን መወጣት ቢያቅታችሁ ለባለቤቱ ተውለት ፤ የግብጽ መንግስት የኮፕቶችን ገዳም ለማደስ 14 ሚሊዮን ዶላር ከውጭ መንግስተት ጋር ተነጋግሮ እርዳታ እንዲያገኙ ሲያደርግ ፤ የእኛው ደግሞ ገዳማችንን ህልውናችንን አፍርሶ ስኳር ፋብሪካ ሊያቋቁም ተነሳ  ይገርማ !!   
·        በስብሰባው ላይ የመንግስት ተወካዮች የስኳር ፋብሪካ ግንባታው ስራ አስኪያጅ እና የሚመለከታቸው አካሎች ከመንግስ በኩል የተገኙ ሲሆን ከአባቶች ወገን ደግሞ ሶስት አባቶች ተወክለው ስብሰባውን አድርገዋል፡፡ ስብሰባው ሲደረግ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ‹‹ በከተሞች አካባቢ የሥኳር ችግር አለ ማህበረሰቡ ስኳር እጅጉን እየተቸገረ ነው፤ ኪሎ ስኳር 18-20 ብር ገብቷል ፤ ይህ ግንባታ ቢከናወን ለሀገርም ለህዝብም ጥሩ ነው የሚል የተሞላውን ዲኩር አሰምቷል ›› ቀጥሎም ምንድነው ችግሩ በማለት ችግሩን ያልታየው ይመስል በጣም በመቆጣት ጥያቄ አቅርቧል ፤ ቁጣ እንኳን አንዳንዴ ከዘር ሊተላለፍ ይችላል አንዳንዴም ደግሞ ግቡን እንዲመታ የሚፈልጉትን ጉዳይ ጽንፍ ይዞ ሲሟገቱ ሳያቁት ሊቆጡ ይችላሉ ፤ በአንድ ጥናት ላይ ስልጣን ያላቻው ሰዎች ለመናደድ ቅርብ ናቸው ይላል ፤ ከአባቶች ዘንድ የተሰጠው ምላሽ ‹‹እኛን ገድላችሁ ፋብሪካውን መስራ ትችላላችሁ ራሳችንን ለሰይፍ ነው ያዘጋጀነው  ፤ እኛ የዋልድባ አፈር ጠባቂ ነን እንጂ  ጠባቂው መድሀኒአለም ነው ፡ ዋልድባን ብታከብሩት ትከበራላችሁ ዋልድባን ብታቀሉት ትቀላላችሁ ብለው በግልጽ ነግሯቿል›› ፡፡ እንዴት ደስ ይላል ቤተክርስትያ በአሁኑ ሰዓት እየተቸገረች ያለችው አቋም የሌለው ሰው በማጣቷ ነው ፤ ከመንግስት ፖሊሲ እና ከእድገትና ትራንስፎርምሽን እቅድ ጋር አብረው ራሳቸውን የሚቀያይሩ ሰዎች ተከባለች ፤ ቤተክርስያን አቋሟ ከመንግስ ጋር አብሮ የሚቀየር አይደለም ፤ የባለስልጣንን ሀሳብ ላይ ተመርኩዞ የሚንቀሳቀስም አይደለም ፤ ስለምናከብረው እና ስለ ምንፈራው ሰው ብለን የምንለዋውጠውም መሆን የለበትም ፤ እንደ ዋልድባ ገዳም  አባቶች ብንኖርም ብንሞትም በእምነታችን ላይ አቋም ያስፈልገናል ፡፡ የእነሱ አቋም ‹‹አይሆንም ራሳችንን ለሰይፍ አዘጋጅተናል ፤ እኛን ሰውታችሁ አላማችሁን ማሳካት ትችላላችሁ›› የሚል ነው አራት ነጥብ፡፡
·        ስብሰባውን በተጨማሪ ለአንድ ቀን ሙሉ መነኮሳት ፤ አቡነ መርቃርዮስ ፤ ባሉበት ተካሂዷል በጊዜው የታረሱትን ቦታዎች ተመልክተዋል ፤ አቡነ መርቃርዮስ ስብሰባውን በጸሎት አስጀምረዋል ፤ በውይይቱ መሀል ላይ ውይይቱ እየጋለ መጥቶ እንደነበር ለማወቅ ችለናል ፤ በሁለቱም በኩል ከረር ያሉ ቃላትን የመመላለስ ነገር ይታይበት ነበር ተብለናል ፤ አባቶች ነገሩ አላምር ሲላቸው ‹‹እናንተ የፈለጋችሁትን ማድረግ ትችላላችሁ ፤ እኛ ይግባኝ ለክርስቶስ ሰጥተናል ለምን ትጨቀጭቁናላችሁ ስራውን እየሰራችሁት አይደል ..››ብሎ ‹አሁንም እንሰየፋለን እንሰየፋለን ብሎ የመነኮሳት ማህበሩ ከስብሰባው ተነሳ ፤ በጊዜው የነበሩ የመንግስት ባለስልጣናት በአባቶች ሁኔታ በጣም መደንገጣቸውንም ለማወቅ ችለናል ፤ 18 ቤተክርስያ ፈርሰው ሸንኮራ ልማት የማይታሰብ ነው ፤ ብለው አቋማቸውን ገልጸውላቸዋል፡ 
·        በትግረኛ ፕሮግራም የገዢው ፓርቲ ሰዎች ቦታው ድረስ በመሄድ የማይመለከታቸውን ሰዎችን በማነጋገር የውሸት ፕሮፖጋንዳ ለህዝቡ አናፍሰውለታል ፤ የገዳሙ አባቶች ልማቱ ላይ እንደማይቃወሙ በማስመሰል የምን ጊዜም ተግባሩ በቴሌቪዠን ያንጸባረቀ ሲሆን ፤ ይህን ጉዳይም አንስተው ጉባኤው ላይ ተነጋግረዋል ፤ የተሰራውን የቴሌቪዥን ፕሮግራም ተመልክተናል ፤ የተሰራው ስራ እኛን አይወክልም የኛም ድምጽ አይደለም ብለዋቸዋል ፡፡ ይህ የህዝብን ድምፅ ለማፈን የሚደረግ ሴራ አጥብቀን እንቃወማለን ፤ ህዝቡ እያለ ያለው ልማታችን አይቋረጥ ገዳማችንንም አትንኩብን እንጂ ለልማት ከሆነ ገዳሙ ይፍረስ የሚል አቋም ያለው ማህበረሰብ የለም ፤ ይህን ነገር በህዝቡ ውስጥ አልሰማንም አላየንምም ብለዋል ፤
·        የልማት ስፍራው ላይ 3 መትረየስ ተጠምዶ በከፍተኛ ሁኔታ ፌደራል ፖሊስ እየጠበቀው ይገኛል ፤ በሁኔታው መወሰን ያልቻሉት ባለስልጣናት ፤ ጉባኤውን ለቅዳሜ አቦይ  ስብሀት ባሉበት ሽሬ ላይ ይደረጋል ብለዋል ፤ አንድ አባት በሰጡት አስተያየት አይደለም አቦይ ስብሀት ጠቅላይ ሚኒትሩም ቢያደራድሩን ከአቋማችን ፍንክች የምንል መነኮሳት አይደለምን ፤ ራሳችንን ለሰይፍ ያዘጋጀን ሰዎች ነን ያለነው ፤ እኛን ገለው ፋብሪካውን መስራት ይችላሉ ብለዋል ፡፡ እኝው አባት አያይዘው ይህችን ቤተክርስትያ እየሸጧት ያሉት አቡነ ጳውሎና መንግስት  ናቸው ማንም አይደለም ብለዋል ፤ በጉባኤው ሂደት ቅዳሜም ምንም አይነት ለውጥ ይመጣል ተብሎ አይጠበቅም ፤ ቅዳሜም ለውጥ ስለሌለ አንሰበሰብም የሚል አቋም እንዳለ ለማወቅ ችለናል ፤

  • እኛ መሳሪያ የለንም ፤ ከናንተ ጋር ግንባር የምንገጥም ሰዎችም አይደለንም ፤ እናንተ በጉልበታችሁ ሁሉን ማከናወን ትችላላችሁ እኛም ለመሰዋት ዝግጁ ነን ይህን ስለቤተክርስትያን የምንቀበለው ሰማእትነት ነው ፤ ዋልድባ በ4 ወንዞች የተከበበች ናት አይኗን፤ እግሯን ጥፍሯ ከአካላቷ አንዲቷም እንድትነካብን አንፈልግም ፤ የበፊት የዛሬ የወደፊት አቋማችን ይህው ነው ብለዋቸዋል ፡
·   እኛ በዚህ ያለነው ማህበረ መነኮሳት አቅም የለንም ማድረግ የምንችለው ለሰይፍ ተዘጋጅተን መቀመጥ ብቻ ነው ብለዋል ፤ አቅም ያላቸው በውጭ የሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስን አማኞች በያሉበት በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት ጥያቄያችን ያቅርቡልን ፤  ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ሀሳባችንን ተጋርተው ከአጠገባችን እዲቆሙ መልእክቴን አስተላልፋለሁ ብለዋል፡፡

አባቶቻችን ይህችን እምነት ይዘው ሁሉ ነገር አልጋ በአልጋ ሆኖላቸው አያውቅም ፤ ለክርስትያን ፈተና የህይወቱ አንዱ ክፍል ነው ፤ ፈተናን መወጣት የሚቻለው በጉልበት ፤ በገንዘብ ፤ ባስልጣን  አይደለም ፤ እንደ ቤተክርስትያናችን አስተምህሮ ፈተናን ለመቋቋም ጾም ፤ ጸሎት ፤ ስግደት እና የትሩፋት ስራዎችን ከፅናት ጋር  መስራት ግድ ይላል ፤ በአሁኑ ሰዓት የኛ ፈተናችን ይህ ነው ፤ ፈተናችንን በድል እንድንወጣ ሁላችን በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ሆነን ከገዳማውያን አባቶቻችን ጎን መቆም መቻል አለብን ፤ እነሱ የመጣውን ሊቀበሉ ወስነው ተቀምጠዋል ፤ ቤተመንግስት ድረስ ሄደው ያተረፉት ስድብ ብቻ ነው ፤ ስለዚህ በጾምና በጸሎት ከገዳማቸው  ሆነው አምላክን ቢለምኑት ጸሎታቸውን እንደሚሰማ ካልሆነም በህይወት እያለን ይህን ማየት ስለማንፈልግ እኛን ገላችሁ መስራት ትችላላችሁ የሚል አቋም ወስደዋል ፤ ቤተክህነቱም ከመንግስት ጎን በመቆም ሊያስማማ ወደ ቦታው ተወካዩን ልኳል ፤ ይህም አለመታደል ነው ፤ እኛስ ምን ማድረግ አለብን ? ለሁላችን የምጠይቀው ጥያቄ ነው፡፡ እስኪ በጸሎት እናስባቸው ፤ ይህንም የፈተና ጊዜ ቤተክርስትያን ታልፈዋለች  አንጠራጠርም ፤


‹‹መካሪ የሌለው ንጉስ ያለ አንድ ዓመት አይነግስ›› ይባላል ፤ እኛ አሁንም የአባቶቻችን ርዕስት ሲፈርስ የምናበት አይን የምንሰማበት ጆሮ የለንም ፤ ዋልድባ ለእኛ ምን ማለት እንደሆነ እንድናስረዳችሁ ከፈለጋችሁ መልካም ፤ ያለበለዚያ በሞላ ቦታ አይናችሁን ከዋድባ ላይ ብታነሱ መልካም ነው ፤ ከእኛ ጋር ሳይሆን የምትጋፈጡት ከባለቤቱ ጋር መሆኑንም አትርሱት ፤ ባለቤቱ ደግሞ የሰማይና የምድር ፈጣሪ መድሀኒዓለም ነው የራሄልን እንባ የተመለከተ አምላክ የእነሱንም ይመለከታል ፤ ዓይንን የፈጠረ አምላክ ያያል ፤ጆሮን የፈጠረ ጌታም ዘንበል ብሎ እሪታችችን ኡኡታችን ይሰማል አንጠራጠርም ፤ በእናንተ ጩህት የሚመጣ ነገር የሰው ጆሮ ማደንቆር እንጂ ሌላ ነገር አይደለም ፤ የቅዱሳንን አጽም እንደ አልባሌ ነገር አትቁጠሩብን ፤ ለእናንተ ምንም ሊሆን ይችላል ለእኛ ግን  ትርጉም ያለው ነገር ነው ፤ ለነገሩ መጠበቅ የሚገባችሁ እናንተ ነበራችሁ ምን ዋጋ አለው የራስን ዝቅ አድርጎ የማየት ክፉ አመል ተጠናውቶናል እናም እኛ አንፈርድም፡፡ ገዳሙን ግን ለቀቅ አድርጉን ፤  ይህን ፅፌ ከጨረስኩኝ በኋላ ገዳሙ እየተጋፈጠ ያለውን  ፈተና አስቤ እንባዬ መጣ...... አይኔንም ሞላው……………

45 comments:

  1. በጣም ኅሊናን የሚፈታተን አሳዛኝ ቃለ መጠይቅ ነው:: የተጠያቂው አባት እርጋታና የሚፈልጉትን በሚገባ መግለጣቸውን ሳስተውለው ተገረምኩ:: ምንም የንደት ምልክት አይታይባቸውም ይሁን እንጅ በጣም ተሰሚና የሚያሳምን አገላለጥ ነው:: የመነኮሳቱ ቆራጥነታቸው፣ ታማኝነታቸውና ተቆርቋሪነታቸው የተለየ ነው:: እንደዚህ ያሉ አባቶችን ያላሳጣን አምላክ ክብር ምስጋና ይድረሰው:: ጎበዝ እነሱ የድርሻቸውን ከሚገባው በላይ እየተወጡ ነው:: እኛ ግን የሚጠበቅብን ጥቂቱን እንኳ እየተወጣን አይደለምና እባካችሁ ተጠያቂው አባት ያሉንን እንኳ እንፈጽም:: የአባቶቻችንን የቋርፍ ደን መንጥሮ ሸንኮራ ሊዘራ እነሱ ምን እንድበሉ ነው:: አይ የመንግስት ጭካኔ:: ምነው ለባእዳን እድገት ታሪክን ኃይማኖትን ማጥፋት ለምን አስፈለገ :: ምነው ለህንድና ለአረብ ከማሰብ ለወገን ማሰብ ቢቀድም:: ምን አይነት የከሃዲዎች ዘመን ላይ ደረስን:: ለነገሩ ደግ አድርጎናል እኛም ዝምታውን አብዝተነው ነበር ጸሎቱንም ትተነው ነበር:: አገራችንን ለወሮበላ ትተን ዝም ብለን ተቀምጠን ነበር እናም ይበለን:: ገና ብዙ እንሰማለን:: እስራኤልን ከባርነት ነጻ ያወጣ አምላክ ማምለካችንን በነጻነት ያደርግልን ዘንድ ፈቃዱ ይሁንልን:: የአባ ጳውሎስን ነገር እንዳው ለሱ እተወዋለሁ::

    ReplyDelete
  2. ከእኛ ጋር ሳይሆን የምትጋፈጡት ከባለቤቱ ጋር መሆኑንም አትርሱት ፤ ባለቤቱ ደግሞ የሰማይና የምድር ፈጣሪ መድሀኒዓለም ነው የራሄልን እንባ የተመለከተ አምላክ የእነሱንም ይመለከታል ፤ ዓይንን የፈጠረ አምላክ ያያል ፤ጆሮን የፈጠረ ጌታም ዘንበል ብሎ እሪታችችን ኡኡታችን ይሰማል አንጠራጠርም

    ReplyDelete
  3. nice our fathers!!!!
    we will follow you!!!
    don't hesitate to scarify your self!!!
    from bahir dar

    ReplyDelete
  4. ይህ መንግስት ቁናው ሞልቶ እድሜውን ሊያሳጥር ነው፡፡ ከአባቶችችን ጋር እንሞታለን፡፡
    ገለታ ከባህር ዳር

    ReplyDelete
  5. Ante Yeabatochachin Amlak!Yenabuten Dem yetebekelik Fetari Egziabeher Hoy!Ebakih siman!Fetineh betihin Tadeg!Abatochachini Nabuten Ayihunu meriwochachinim Akiabin ayimiselu Elizabelim Hail atagign! hulunim Beselam Enifetaw zenid Lenegesitatum Libona sitilin Abatochachinini Menekosatunim Atsinalin.AMEN!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  6. ከአባቶችችን ጋር እንሞታለን፡፡

    Those whose time expires/reaches please leave our country!

    Awassa

    ReplyDelete
  7. EMEAMLAKIN AHUNIS ABEZAHIWU MELES ZIENAWI BEHAYIMANOTIEMA ENDATIMETA wa wa wa biyalehu!

    ReplyDelete
    Replies
    1. የ መነኩሳቶች ሞት የሁሉም ortodox ሞት ነውና ይታሰብበት!
      የእኛም የ ወጣቶች ሞት ነው!

      "እርስቴን አለቅም/አልቀይርም!" ብሂለ አበው

      መብት ከፋለ (Gondar)

      Delete
    2. ውሳኔችን የአባቶቻችን ነው::
      Mebit(motta)

      Delete
  8. Binmotm bininorm ye egziabher new.

    ReplyDelete
  9. bewunet betam yemiyasazn neger new engnam yhin neger zm blen mayet anchilm.
    eskemechereshawu dres enwagalen enji.

    ReplyDelete
  10. fetenaw eyechemere lewitet endemitega temari honoal yemengist ena yeabatochachin neger. abet tsinatachew abatoche ahunim ende enante yalu abatochin bezih kifu zemen kebetekrstian ras enkuan yaltasebe milash sisetu mesmat endet yasdestal. Balebetu Medhanealem lezih tegadloachihu waga sikefil abizto yisetachihual. Bertulin bewsaneachihu tsentachihu gifubet. yeKidusan Amlak melkamun yaseman Amen. Bemechereshaw gin malet yemifelgew hizibe kirstian kalen lay yakmachinin endiniredachew yehone menged bitaseb. beketita lenesu bemidersibet melku malet new.
    Alfo Ayichew

    ReplyDelete
  11. But to me the topic አንድ አድርገን and the content " በእዚያ ያሉ ሰዎች (በሽሬ) ለእኛ ጥሩ አመለካከት የላቸውም" and the whole sprite of Orthodox doesn't support such segregation and labeling. The fathers know those people in ሽሬ or AXUM as their credentials for our basic religion. So, i strongly doubtfull such wording from a father or at least servant of God. But, i strongly support the idea if that holds true?

    May God save our Orthodox.

    ReplyDelete
  12. Giragn mehamdena yodit gudit kezih yebelete min adrgewal?

    ReplyDelete
  13. በሚዛን ተመዘነህ ቀለህም ተገኘህ ሰለዚህ መንግስትህ ካንተ ትሄዳለች!!!

    አንተ ውሸታም አስመሳይ መንግስት ስማኝ‼! በማን ላይ ቁመሽ እግዜርን ታሚለሽ ይላል ያገሬ ሰው አሁን በአውነት ይህች ሀገር በአንተ ፖሊሲና አስተዳደር የቆመች ይመስልሃል? አይ አለማወቅ‼ እነደነዚህ ባሉ ገዳሞች የሚኖሩት አባቶቻችን በሚፀልዩት ፀሎት በረከት ነው ሆዳችንን ሞልቶ የሚያድረው፡፡ እሰኪ በሞቴ የመንግስት ሠራተኞች በቀን ስንት ስዓት በስራ ላይ ያሳልፋሉ? የሚሰሩት አጥተው አይደል ቁጭ ብለው የሚውሉ ግን እንጀራ ይበላሉ ይህ እንጀራ ሳይሰራ ከየት መጣ? በረከት ይሉሃል ይህ ነው፡፡
    የቅርስ ቀበኛ‼!የቅርስ ቀበኛ‼!የቅርስ ቀበኛ‼!የቅርስ ቀበኛ‼! የቅርስ ቀበኛ‼!
    የአሰተዳደር ሰላይ፣
    የውሰኔ ወላዋይ፡፡
    የመድረክ አንበሳ፣
    የፖሊሲ ሬሳ፡፡
    የሃይማኖት አጥፊ፣
    የጊዜው ቀጣፊ፡፡
    ውድ የተዋህዶ ልጆች እባካችሁ እርስታችንን እንጠብቅ? ዝምታችን ለምንድን ነው በየቤ/ክርስቲያናችን ድምፃችንን እናሰማ
    ወይኔ አባቶችችን የእሳት ልጅ አመድ አንሁን
    ገ/ስላሴ ከባህር ዳር

    ReplyDelete
  14. eyasy gebremichaelMarch 17, 2012 at 6:44 AM

    Goverment should change this idea
    Government should know the power of the governement is less than the power of God
    Government shold know Ethiopian orthodox people stand infront of him if he respect our religion..

    ReplyDelete
  15. THEIR IS ONE IMPORTANT THING THAT ETHIOPIANS NEVER UNDERTAND.THERE SHOULD BE AN EQUIVALENT AND OPPOSITE REACTION FOR A CERTAIN ACTION.THIS IS NEWTON'S LAW.A NATURAL LAW.I CAN RECOMMEND A REACTION LIKE BURNING THE TRACTORS PLAUGHING,BURNING CAMPS,ASSASINATING THE DECISION MAKING PEOPLE,ABDUCTING THEIR FAMILY MEMBERS ETC...PROVIDED THAT THERE ARE PEOPLE WILLING TO SACRIFY FOR A SPECIFIC PURPOSE.SOME ONE IS NOT NOT SUPPOSED TO HAVE A GUN TO DO THESE.ELSE,WE WILL SEE THAT EVERYTHING WILL BE DONE AS PLANNED BY THE GOV'T BY ARRESTING SOME OF THE OPPOSING LEADERS.

    ReplyDelete
  16. የስኳር ፋብሪካ ብዙ ውኃ ይጠቀማል። የዚህ ውኃ ፍሳሺ (በእንግሊዝኛ ዌስት የሚባለው) በየአንዳንዱ ሊትር ፍሳሺ ውስጥ አንድ ሺህ አምስት መቶ ባዮኬሚካል ኦክስጂን ዲማንድ አለው። ይህ ማለት ይህ ፍሳሺ የፈሰሰበት ቦታ ሁሉ በተለይ ውኃ ያለበት ነገር በዚህ ፍሳሺ ይታኜክና ህይወት ያላቸው ነገሮች በሱ አካባቢ መኖር አይችሉም። በተለይ በውሃ ውስጥ እና በውሃ ዳር የሚኖሩ ህይወት ያላቸው ነገሮች አደጋ ላይ ይወድቃሉ። በዚህ ላይ ከስኳር ፋብሪካ የሚፈስ የተበላሸ ዘይት፣ ከባጋሴ መቀቀያው የሚወጣው ሳልፈርና ናይትሮጂን የሰፈሩን አየር ይበክለዋል። ይህ ፋብሪካ በዋልድባ ከተሠራ አራቱ የዋልድባ ወንዞች ከ ሀያ አምስት እስከ አምሳ አመት በሚደርስ ጊዘእ ውስጥ ይደርቃሉ ቦታውም የሚገለማ ሺታ የሚወጣበት ይሆናል። የዋልድባ ደን ይደርቃል። የተቀደሰው የዋልድባ ገዳም ውበቱና መልካም አየሩ ብቻ ሳይሆን በአካባቢው የሚኖሩ ገበሬዎች ወደፊት በዛ የመኖር እድል አይኖራቸውም። የስኳር ፋብሪካው ጥቂት ሰዎች ለጊዜው ሊቀጥር ይችላል። ከትንሺ ጊዜ በኋላ ግን ሥራውም አይኖርም ህይወትም በዛ አይኖርም። ነገሩ ሁለት ጊዜ ጥፋት ነው።

    የኢትዮጵያ መንግሥት እውቀት ስለሚጎድለው ብዙ ጥፋቶችን እያደረሰ ነው። የስኳር ፋብሪካ ሊሠራበት የሚችል ስንት በረሃ ሞልቶ የለምን? እነዚህ ሰዎች ስንት መሬት ለአረብና ለህንድ በነጻ እየሰጡ ዋልድባን ምን አስመኛቸው? ወይ ጉድ ወይ ጉድ። አቤቱ ቸሩ መድኃኒአለም - ሊትዮጵያ ድረስላት ዘንዶው ሊውጣት አፉን ከፍቷልና፤ ያላንተ መዳህኒት የላትምና፥ ንጉሥ ሆይ ቶሎ ና።

    ReplyDelete
  17. ቅዱሳንን መነካካት አያስፈልግም….መዓት በሀገር እና በእራስ ላይ ለማምጣት ከሆነ በረቱበት፡፡ የቤተክርስቲያን አምላክ ይፋረዳችሁ…..እባካችሁ የቤተ ክህነት ሰዎቸህ ቤተ ክርስቲያንን አሳልፋችሁ አትደራደሩ …ከ ሙስሊሞች እነ ኳ ተማሩ… ቸር ያሰማን

    ReplyDelete
  18. Melaku, Addis AbabaMarch 19, 2012 at 8:39 AM

    Behaimanotma wegenie keldi yelem. Ene Meles Zenawi Zemenachew eyalekechi sayhon aykerim.
    Yemidir ena yesemay Amlaki hoy anten yemiawuku yehager meriwochi ena anten befitsum libachew yemiamelku yebete kiristian meriwochi siten.
    Melaku, Addis Ababa

    ReplyDelete
  19. Please God see us????????

    ReplyDelete
  20. I apprciate the stand of our fathers.Now the big hayena is ready to eat the flesh of our fathers as well as the bones of holy fathers. You Guys what do you expect from those peoples who havn't religious like Meles and Aba poulos because they are not from our home church,EOTC. You do not know this?

    So let us make ready ourselves at the back of our monks? I appreciate thier decition.
    The other thing that Nobody didn't doesn't expect milk from the scorpions (Meles & his followers). They are selling the property of our churches and Ethiopia.

    Let God think over our church and brings durable solution for all of us.
    God bless Ethiopia!!!!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  21. Egziabhare kega gare yehunegi enama akeme yalaneme huluneme chaye amelake yemlektane

    ReplyDelete
  22. egeg betam yasazenal. yeabatochachenen erest masenekat ayedelem lemenkat masaseb yelebenem. selezi bebetachen lay yemifesemew bedel lekom yegebal

    ReplyDelete
  23. ሆድን ያቃጥላል፣ሆድን ይበላል !!! ልብን ይሰብራል!!!ያሳዝናል!!!የአይን እምባ ያጎርፋል !!!የቤተ ክርስትያን ልጅ ሁሉ አንድነቱ ልያሳይ ፤ሆ!!! ሆ!!!ሆ!!!እንዲልና እውነተኛ የክርስቶስ አካል መሆኑ የምያሳይበት ፤በጾም፡ በጸሎት የሚተጋበት፡እየሰገደ የምያለቅስበት ፡በመሪዎቻችን አድሮ ቤተ ክሪስቲያን ለማጥፋት የተነሳው ዲያብሎስ የምናሸንፍበት ለኛ የተሰጠ በረከት የያዘ ፈተና ነው። እርግጠኛ ነኝ ሁሉም ክርስቲያን በዚህ ነገር "የ እግዚአብሔር የተባለ እቃ ሁሉ ለብሶ ከተነሳ " እንደ አባቶቻችን ጸጋ እናገኝበት አለን ። በ እያለንበት ይሁን ወደ ሚመለከተው አካል ሆ!!! ብለን ካልተነሳን ግን
    1፡ስለ ክርስቶስ አልመሰከርንም እሱም በፍርድ ቀን በአባቱ ፊት አይመሰክርልንም ፡
    2፡ሁሌ የምያስጨንቀኝ ስለ ቤተ-ክርስትያን ነው የሚለው የ ሃዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ ቃል ሰተናል።
    3፡ራሳችን እናጠፋለን እያንዳንዳችን ቤተ-ክርስትያን ነንና።
    4፡ሃይማኖታች ትዳክማለች መክሊታችን ደብቀናልና እንወቀሳለን ።
    5፡እውነተኛ ክርስትያኖች መሆናችንን ያሳስባል።ወዘተ...
    ለመሪዎቻችንም እንጸልይላቸው ልቦናቸውን እንድያስተውል ፡ንስሃም እንዲደቡበት ።
    እግዚአብሔር ስጋውና ደሙ የሚፈተትባቸው መኖርይዎቹ ይጠብቅ።
    የአገልጋዮቹ መኖኮሳት ጭሆትና ልቅሶ ይስማ።
    ሃይማኖታችንና ቤተ ክርስትያን ገዳማት ይጠር።
    ስብሃት ለ እግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ። አመን

    ReplyDelete
  24. ሆድን ያቃጥላል፣ሆድን ይበላል !!! ልብን ይሰብራል!!!ያሳዝናል!!!የአይን እምባ ያጎርፋል !!!የቤተ ክርስትያን ልጅ ሁሉ አንድነቱ ልያሳይ ፤ሆ!!! ሆ!!!ሆ!!!እንዲልና እውነተኛ የክርስቶስ አካል መሆኑ የምያሳይበት ፤በጾም፡ በጸሎት የሚተጋበት፡እየሰገደ የምያለቅስበት ፡በመሪዎቻችን አድሮ ቤተ ክሪስቲያን ለማጥፋት የተነሳው ዲያብሎስ የምናሸንፍበት ለኛ የተሰጠ በረከት የያዘ ፈተና ነው። እርግጠኛ ነኝ ሁሉም ክርስቲያን በዚህ ነገር "የ እግዚአብሔር የተባለ እቃ ሁሉ ለብሶ ከተነሳ " እንደ አባቶቻችን ጸጋ እናገኝበት አለን ። በ እያለንበት ይሁን ወደ ሚመለከተው አካል ሆ!!! ብለን ካልተነሳን ግን
    1፡ስለ ክርስቶስ አልመሰከርንም እሱም በፍርድ ቀን በአባቱ ፊት አይመሰክርልንም ፡
    2፡ሁሌ የምያስጨንቀኝ ስለ ቤተ-ክርስትያን ነው የሚለው የ ሃዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ ቃል ሰተናል።
    3፡ራሳችን እናጠፋለን እያንዳንዳችን ቤተ-ክርስትያን ነንና።
    4፡ሃይማኖታች ትዳክማለች መክሊታችን ደብቀናልና እንወቀሳለን ።
    5፡እውነተኛ ክርስትያኖች መሆናችንን ያሳስባል።ወዘተ...
    ለመሪዎቻችንም እንጸልይላቸው ልቦናቸውን እንድያስተውል ፡ንስሃም እንዲደቡበት ።
    እግዚአብሔር ስጋውና ደሙ የሚፈተትባቸው መኖርይዎቹ ይጠብቅ።
    የአገልጋዮቹ መኖኮሳት ጭሆትና ልቅሶ ይስማ።
    ሃይማኖታችንና ቤተ ክርስትያን ገዳማት ይጠር።
    ስብሃት ለ እግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ። አመን

    ReplyDelete
  25. የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተለመደ ዉሸቱን እየዋሸ ይገኛል:: እስኪ እዉነት ከሆነ ቤተ ሚናስ ያሉ አባቶችን በቀጥታ ያለዉን ሁኔታ ዘግበዉ ለህዝቡ አላደረሱም ለመሆኑ የገዳሙ የእርሻ ቦታ የት ነዉ ያለዉ የሚለዉን ጉዳይ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያጣራና ይግለፅልን ማይ ሐረገፅ ጊዮርጊስ፣ እጣኑ ማርያም፣ ደለሳ ቆቃ አቡነ አረጋዊ፣ ማይ ገባ ሚካኤል የሚባሉ ከ እያንዳንዳቸዉ ከ300-400 መናንያን የሚኖሩባቸዉና ለገዳሙ አብይ የእርሻ ቦታዎች መንግስት በሚያደርሰዉ ግፍ የዋልድባ ገዳማት የሚያጣቸዉ ቦታዎች ይሆናሉ:: መንግስት ለምንድነዉ የራሱ የሆኑ ሰዎችንና በምንፍቅና ህይወት ዉስጥ ያሉትን ለምስክርነት የሚያቀርበዉ:: እኛ እያለነ የምንገኘዉ እርስታችንን አትንኩብን ነዉ ሌላ ፓለቲካዊ አጀንዳ የለንም! እኛ እግዚአብሔርን ይዘን እንቃወማለን እነርሱም ምድራዊ ሰራዊታቸዉንና የጦር መሳሪያቸዉን ይዘዉ ያስፈራሩናል! አሸናፊዎችን እግዚአብሔር ያዉቃል!!

    ReplyDelete
  26. አቤቱ አምላክ ሆይ የወያኔን አገዛዝና የ አሪዮስ ልጅ ፓትሪያርክ ጳውሎስን መጨረሻቸውን ለማየት ጓጉቺያለሁ፡፤

    ReplyDelete
  27. Kega gara yalelew kenesu yebeletal

    ReplyDelete
  28. amelake esraiel hoy ebakeh kezeh hulu gud awetan ega legocheh gena bezu neger keabatochahin enemaralen kebeteh bereketin enagegalen senel endeh aynet lemamen mekbed neger ataseman yeserawit geta maren erkachinen atsekeren.......

    ReplyDelete
  29. egzihabeher amelak hoy ebakeh kezeh hulu meat awetan betachenin asalfeh atesetben gena kebetachin bezu bereket algegenim ebakeh tareken amelakchin.

    ReplyDelete
  30. GOD will see all these maltreatments!

    ReplyDelete
  31. ከቤተ ክህነት እሰከ ፓትረያሪኩ የተዘረጋዉ የመለስ ወጥመድ የቤ/ክርቲያንን መብት እየሸረሸረዉ
    አሳልፎ ሊሰጥ ነዉ፡፡ ዝም አንልም
    ገ/ሀሃነና ከበባ/ደዳረር

    ReplyDelete
  32. ይህ በገዳሙ ላይ የሚደረገው የእርሻ ልማት ሳይሆን በኦርቶዶክስ ክርስትና የመጣ ጥፋት በመሆኑ አጥብቀን እንቃወመዋለን።
    የሺወርቅ

    ReplyDelete
  33. yohannes abiy ewnetuMarch 24, 2012 at 10:43 PM

    We have to keep our monastry ,,,

    ReplyDelete
  34. yekeresetos lejoche zem ateblu.bekberwe demu yagengnwe setota lenezrefe ayegbam!!!

    ReplyDelete
  35. የህን ክፉ ግዜ በቸርነቱ ይጠብቀን

    ReplyDelete
  36. ከአሁን ብሁዋላ ከመንግስት ምንም አንጠብቅ፡፡ ወይ አለማዊነትን ወይ ሀይማኖታችንን እንምረጥ!!

    ReplyDelete
  37. ለሰለሞን ጥበብን የሰጠህ ጌታ ከዚህ ሁሉ መዓት በጥበቡ ያውጣን።
    ኤፍሬም

    ReplyDelete
  38. ይህ መንግስት ቁናው ሞልቶ እድሜውን ሊያሳጥር ነው፡፡ ከአባቶችችን ጋር እንሞታለን!!

    ReplyDelete
  39. god is with us, nat with thieves. the end is nat far.

    ReplyDelete
  40. mengest litefa sil kehayamanot gar yetalala

    ReplyDelete
  41. Yeabatochachin amlak yefareden meles mewrejaw dersoal.

    ReplyDelete
  42. አንድ እንሁንና አንድ ቀን ‹‹ጸሎተ ምህላ›› እንዲሰጥ ቀጠሮ ተደርጎ አዋጅ ይነገር ያኔ እግዚአብሔር ይነሳል፤ የማይታየው ይታያል፣ የማይገለጠው ይገለጣል፣ የተሰወረው ይታያል፡፡ የጠመመው ይቀናል፤ የቀናውይ ይገለጻል፡፡ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ያኔ ይሆናል፡፡ ልባችንን አንጽተን ፣ እግዚአብሔር እንደመረጣቸው መነኮሳት፣ ጻድቃን፣ ቅዱሳን፣ ፍጹማን ደናግል፣ እንደስውራን፣ እግዚአብሔር እንደሚያቃቸው እኛ እንደማናቃቸው እርሱ ቃልኪዳን እንደሰጣቸው ለእግዚአብሔር ጥሩ ዕቃዎች ሆነን፣ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የመስቀሉን አርአያ ትምህርት ‹‹ የሚሰሩት አያውቁምና ይቅር በላቸው›› የምትለውን ትርጉም ተገንዝበን ጠላታችን ዲያብሎስ ይቺን እምነትና ሃይማኖት ሊያጠፋ የመጣ መሆኑን ተገንዝበን ለዲያብሎስ መሳሪያ ሆነው የመጡብንን ሁሉ እነርሱ ሳይሆኑ የጠላት ዲያብሎስ ውጊያ መሆኑን ተረድተን ፣ እንዳባቶች ትምህርት ፣ እንደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ እርትኢት ፤ በክርስቶስ ክርስቲያን ነንና በእግዚአብሔር የሚያምን አያፍርም፤ አይፈራም፤ በእግዚአብሔር የሚያምን በእግዚአብሔር ሁሉን ነገር ያደርጋል፡፡ ትምክታችን እግዚአብሔር ነውና፤ ይህችን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ያቃለለ፤ የቤተክርስቲያንን ጥፋት የሚፈልግ ሁሉ፤ ይጠንቀቅ ዋላ መጨረሻው አያምርምና፤ ትንቢቱ ይፈጸምበትና ፤ ይቺህ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት የኢትዮጵያ፤ ሀገሯ፣ የኢትዮጵያ መልኳ ፣ የኢትዮጵያ ኃይሏ፣ የኢትዮጵያ ጋሻዋ፣ የኢትዮጵያ ምሶሶዋ፣ የኢትዮጵያ አጥሯ፣ የኢትዮጵያ ምግቧ፣ የኢትዮጵያ ንጽሕናዋ፣ ኢትዮጵያ ለእግዚአብሔር የምትታዘዝበት ድልድይ፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት ምድሯ፤ ስለሆነች አይምሮ ያለው ያስተውል፤ የሚያስተውልም ይንጠንቀቅ፤ ከምድራውያን ሳይሆን ከእራሱ ከባለቤቱ ከአምላክ ጋር ነውና የሚጋጨው ይጠንቀቅ፤ ይህ ለሁሉ ተነግሯል፡፡ ቤተክርስቲያንን ሊያጠፉ ለተዘጋጁ ማስጠንቀቂያ ነውና ሞት መች የሚመጣ መሆኑ አናውቅምና እናስተውል፡፡
    ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይባርክር!
    ብሥራተ ገብርኤል

    ReplyDelete
  43. አንድ እንሁንና አንድ ቀን ‹‹ጸሎተ ምህላ›› እንዲሰጥ ቀጠሮ ተደርጎ አዋጅ ይነገር ያኔ እግዚአብሔር ይነሳል፤ የማይታየው ይታያል፣ የማይገለጠው ይገለጣል፣ የተሰወረው ይታያል፡፡ የጠመመው ይቀናል፤ የቀናውይ ይገለጻል፡፡ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ያኔ ይሆናል፡፡ ልባችንን አንጽተን ፣ እግዚአብሔር እንደመረጣቸው መነኮሳት፣ ጻድቃን፣ ቅዱሳን፣ ፍጹማን ደናግል፣ እንደስውራን፣ እግዚአብሔር እንደሚያቃቸው እኛ እንደማናቃቸው እርሱ ቃልኪዳን እንደሰጣቸው ለእግዚአብሔር ጥሩ ዕቃዎች ሆነን፣ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የመስቀሉን አርአያ ትምህርት ‹‹ የሚሰሩት አያውቁምና ይቅር በላቸው›› የምትለውን ትርጉም ተገንዝበን ጠላታችን ዲያብሎስ ይቺን እምነትና ሃይማኖት ሊያጠፋ የመጣ መሆኑን ተገንዝበን ለዲያብሎስ መሳሪያ ሆነው የመጡብንን ሁሉ እነርሱ ሳይሆኑ የጠላት ዲያብሎስ ውጊያ መሆኑን ተረድተን ፣ እንዳባቶች ትምህርት ፣ እንደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ እርትኢት ፤ በክርስቶስ ክርስቲያን ነንና በእግዚአብሔር የሚያምን አያፍርም፤ አይፈራም፤ በእግዚአብሔር የሚያምን በእግዚአብሔር ሁሉን ነገር ያደርጋል፡፡ ትምክታችን እግዚአብሔር ነውና፤ ይህችን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ያቃለለ፤ የቤተክርስቲያንን ጥፋት የሚፈልግ ሁሉ፤ ይጠንቀቅ ዋላ መጨረሻው አያምርምና፤ ትንቢቱ ይፈጸምበትና ፤ ይቺህ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት የኢትዮጵያ፤ ሀገሯ፣ የኢትዮጵያ መልኳ ፣ የኢትዮጵያ ኃይሏ፣ የኢትዮጵያ ጋሻዋ፣ የኢትዮጵያ ምሶሶዋ፣ የኢትዮጵያ አጥሯ፣ የኢትዮጵያ ምግቧ፣ የኢትዮጵያ ንጽሕናዋ፣ ኢትዮጵያ ለእግዚአብሔር የምትታዘዝበት ድልድይ፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት ምድሯ፤ ስለሆነች አይምሮ ያለው ያስተውል፤ የሚያስተውልም ይንጠንቀቅ፤ ከምድራውያን ሳይሆን ከእራሱ ከባለቤቱ ከአምላክ ጋር ነውና የሚጋጨው ይጠንቀቅ፤ ይህ ለሁሉ ተነግሯል፡፡ ቤተክርስቲያንን ሊያጠፉ ለተዘጋጁ ማስጠንቀቂያ ነውና ሞት መች የሚመጣ መሆኑ አናውቅምና እናስተውል፡፡
    ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይባርክር!
    ብሥራተ ገብርኤል

    ReplyDelete